ዳሰሳ ዘ ማለዳ (ጥር 29/2012)

Views: 408

ከእስር የተፈቱ 75 ኢትዮጵያውያን ወደ አዲስ አበባ ሊገቡ ነው

 

ከህገ-ወጥ ስደት ጋር በተያያዘ በታንዛኒያ መንግስት ቁጥጥር ስር ውለው በተለያዩ እስር ቤቶች ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን መካከል 75ቱ ነገ ጠዋት ጥር 30/2012  አዲስ አበባ እንደሚገቡ በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ገለጸ፡፡በሀገሪቱ ታስረው የነበሩትን 1443 ዜጎችን ኢምባሲው በማስፈታት ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ  ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱ ነው ኢምባሲው  ያስታወቀው። በቀጣዩ ሳምንት ከረቡዕ ዕለት  ጀምሮ የተቀሩትን ዜጎች የማጓጓዝ ስራው ይቀጥላል ተብሏል። (ኢዜአ)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት አባላት ሆነው መመረጣቸው ተነገረ፡፡ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደተገኘው መረጃ ከሆነም  ኹለቱ አገራት ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት የምክር ቤቱ አባል ሆነው እንደሚያገለግሉ ተጠቀሷል ፡፡(ኢቢሲ)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት አየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚያደርጉትን በረራ ማቋረጣቸው ተቀባይነት እንደሌለው የአፍሪካ ህብረት የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል ገለፀ።እስከአሁንም በአፍሪካ በቫይረሱ የተጠቃ አንድም ሰው አለመኖሩን የማዕከሉ ዳይሬክተር ጆን ንኬንጋሶንግ አረጋግጠዋል ።ይሁን እንጅ በሁሉም የአፍሪካ ህብረት አባል ሃገራት ቫይረሱ ወደ አገራቸው እንዳይገባና ምናልባት ቢገባ በምን መልኩ መቆጣጠር እንደሚገባ ጥብቅ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። ወደ ቻይና ቀጥታ በረራ ያላቸው አንዳንድ የአፍሪካ አገራት በረራ ማቆማቸውን በመናገረ ይህ ተቀባይነት የለውም ፤ ትክክለኛው  አማራጭ ጥንቃቄ ማድረግ ብቻ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡(ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

ሕብረተሰብ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ የሚዲያ አዘጋገቦች ሲኖሩ፤ ገና ለገና መማር አለብን እያልን ሕብረተሰቡን የሚጎዳ ቀጥተኛ ነገር ሲፈፀም ዝም አንልም ሲሉ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር  ጌታቸው ድንቁ (ዶ/ር) ገለፁ። ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ የቁጥጥር ሥራ እየሰራን መዝግበን እየያዝን በየወሩ መጨረሻ በቁጥር የተደገፈ ሪፖርት ለየሚዲያ ተቋማቱ እንሰጣለንም ብለዋል(ቢቢሲ አማርኛ )

……………………………………………………………………………………………………

በአማራ ክልል በ421 ሚሊየን ብር 200 አዳዲስ የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ ሊጀመር መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።በክልሉ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ከተያዙ 118 ነባር የመስኖ ፕሮጀክቶች መካከል 89ኙ እስከ ቀጣዩ መጋቢት 30/2012  ድረስ እንደሚጠናቀቁ ተነግሯል፡፡በመጋቢት ወር ይጠናቀቃሉ ለተባሉ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያም ከ142 ሚሊየን ብር በላይ በጀት የተመደበ ሲሆን ፕሮጀክቶቹ ተጠናቀው ወደ ሥራ ሲገቡ 219 ሺህ 274 ሄክታር መሬት ያለማሉ ተብሎም ይጠበቃል።በግንባታ ሂደት ላይ ከሚገኙት ፕሮጀክቶች በተጨማሪ 421 ሚሊየን ብር በጀት የተመደበላቸው 200 ዘመናዊ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ እንደሚጀመርም በቢሮው የመስኖ መሐንዲስ የሆኑት  ኃይሉ እንግዳየሁ አስታውቀዋል።(ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበር ‹‹ፖለቲከኛም ይሁን አክቲቪስት የሁለት ሀገር ፓስፖርት ይዞ ሀገር መበጥበጡን ሊያቆም ይገባል›› ሲል የፊታችን የካቲት 3/2012  የሚካሄደውን የሰላም ኮንፍረንስ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ላይ አሳሰበ፡፡በውጪ ሀገር እየኖሩ የሀገር ውስጥ ሰላምን ማሳጣት መቆም እንዳለበትም የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ እንድሪስ መሀመድ ተናግረዋል፡፡ሁሉም ዜጋም ለሀገር ሰላም የበኩሉን አስተዋፅኦ ሊያደርግ ይገባልም ብለዋል፡፡(የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com