ሚኒስትሯ ከዱባዩ “ዲፒ ወርልድ” ጋር በሎጅስቲክስ ዘርፍ በትብብር ለመሥራት ከሥምምነት መድረሳቸውን አስታወቁ

0
941

ሰኞ ጥር 16 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ ከ“ዲፒ ወርልድ” ሊቀ-መንበርና ሥራ አስፈጻሚ ሱልጣን አሕመድ ቢን ሱላዬም ጋር በዱባይ ፍሬያማ ውይይት ማካሄዳቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሚኒስትሯ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፣ በቀጣይ ከአገልግሎት ሠጪ ድርጅቱ ጋር በሎጅስቲክስ ዘርፍ በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ሂደቶች ላይ ተወያይተው አጋርነታቸውን ለማሳደግ ሥምምነት ላይ መድረሳቸውን ጠቁመዋል፡፡

“ዲፒ ወርልድ” መቀመጫውን በዱባይ እና በተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ያደረገ ተቋም ሲሆን በዓለም ዐቀፍ ደረጃ የጭነት፣ የወደብ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የንግድ ሎጀስቲክስ አገልግሎት በማቅረብ እና ንግዱን በማሳለጥ ይታወቃል፡፡
_____
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here