ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመጪው ጥር 24 እስከ ጥር 27 ይሰጣል

0
676

ሰኞ ጥር 16 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመጪው ጥር 24 እስከ ጥር 27 እንደሚሰጥ ተገለፀ።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዲሁም የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በትምህርት ሥርዓቱ ላይ ያደረሰው ተፅእኖ ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል።

በተለይም ወረርሽኙ ወደአገር ከገባ በኃላ እና በትግራይ ክልል ጦርነት ከተነሳ በኃላ የዓመቱ መርሀግብር በእጅጉ ተናግቷል።

ከጥቂት ወራት በፊት ብሄራዊ ፈተና የወሰዱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እስካሁን ውጤት ያልተነገራቸው ሲሆን በዚህም ያለትምህርት ወራትን ለማሳለፍ ተገደዋል።

እስካሁን የፈተናው ውጤት ይፋ የሚደረግበትም ቀን አልታወቀም።

በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች በፀጥታ ምክንያት የ12ኛ ክፍል ፈተና መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ከመጪው ጥር 24 እስከ ጥር 27 ቀን 2014 ለፈተና ይቀመጣሉ ተብሏል።

በትግራይ ክልል ፈተና መቀመጥ የነበረባቸው ተማሪዎች በጦርነት ምክንያት ላለፉት ዓመታት በአግባቡ ለፈተና መቀመጥ አልቻሉም።

በአጠቃላይም 58 ሺህ 936 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ ይገመታል።
_______
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here