ሰኞ ጥር 16 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የመስኖ ግድብ ግንባታዎች እንዳይቆራረጡ ተቋራጮች ሲሚንቶ በቀጥታ ከፋብሪካዎች እንዲወስዱ የሚያስችል መግባባት ላይ መደረሱን የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገልፀዋል።
የመስኖ ግድብ ግንባታዎች ያለባቸውን የሲሚንቶ እጥረት በተመለከተ በዛሬው እለት ከመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መህመድ ጋር በመሆን ከሲሚንቶ አምራቾች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል።
በዚህም “በቆላማው የአገራችን ክፍሎች የሚደረጉ የመስኖ ግድብ ግንባታዎች እንዳይቆራረጡና በተገቢው ፍጥነት እንዲጠናቀቁ ለማስቻል ግንባታውን የሚያከናውኑ ተቋራጮች ሲሚንቶ በቀጥታ ከፋብሪካዎች እንዲወስዱ ማድረግ በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ከአምራቾቹ ጋር መግባባት ላይ ደርሰናል” ሲሉ ገልጸዋል።
_______________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n






