የኦሮሚያ የግብርና ሽግግር ምክር ቤት ተመሰረተ

0
941

በኦሮሚያ ክልል በግብርና ዘርፍ እየተመዘገበ ያለውን ለውጥ ተቋማዊ የሚያደርግ የሽግግር ምክር ቤት ተመሰረተ።

በክልሉ ግብርናን ለማዘመንና በተቋማዊ አደረጃጀት ለመምራት አላማ ያደረገ መድረክ በአዳማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የግብርና ሚኒስትር ዑመር ሁሴንን ጨምሮ የምርምር ተቋማት፣ ዩኒቨርሲቲዎችና የተለያዩ ድርጅቶች ተወካዮች እየተሳተፉ ነው።

በዚህም እየተከናወነ በሚገኘው መድረክ ላይ የክልሉ ግብርና ሽግግር ምክር ቤት በይፋ ተመስርቷል።

ምክር ቤቱ የፌዴራልና የክልሉ የግብርና ምርምር ማዕከላት፣ ዩኒቨርሲቲዎችና የምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዞች፣ በየደረጃው ያሉ የግብርና ሴክተሮችን በአባልነት ያቀፈ ነው ተብሏል።

ክልሉን በስንዴ፣ በገብስ፣ በጤፍ፣ በጥራጥሬ፣ በቡና፣ በአትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ በሰባት ክላስተሮች በማደራጀት በግብርና ዘርፍ እየተዘገበ ያለውን ሽግግር ለማሳካት ምክር ቤቱ መቋቋሙ ተመላክቷል።

የምክር ቤቱ መቋቋም የቴክኖሎጂ አቅርቦት፣ መካናይዜሽን፣ መስኖ፣ የተሟላ የኤክስቴንሽን አገልግሎት፣ የገጠር ፋይናንስ አቅርቦት፣ ገበያ ተኮር ምርቶች፣ በምግብ ራስን መቻልና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ለማሳደግ አቅም እንደሚፈጥርም መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

ከውጭ የሚገቡ የግብርና ምርቶችን በአገር ውስጥ መተካትና የተፈጥሮ ሀብት ልማትና አካባቢ ጥበቃ ሥራዎች በምክር ቤቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሥራዎች መሆናቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ ሀላፊ አብዱረህማን አብደላ አስታውቀዋል።
_______________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here