መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን ለመጎብኘት ጅግጅጋ ገቡ

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን ለመጎብኘት ጅግጅጋ ገቡ

ማክሰኞ ጥር 17 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር (ዶ/ር) ዐቢይ አህመድ በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን ለመጎብኘ ጅግጅጋ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጂግጂጋ ሲደርሱም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራው የልዑካን ቡድን በክልሉ በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን በመጎብኘት የሰብዓዊ ድጋፍ ክንውኖችን ይገመግማል ይጠበቃል።

በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ከ230 ሺህ በላይ እንስሳት ሲሞቱ፣ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ አርብቶ አደሮች የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ከክልሉ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች