ማክሰኞ ጥር 17 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በጠቅላይ ሚኒስትር (ዶ/ር) ዐቢይ አህመድ የተመራ የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ልዑክ ከክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ተፈናቃዮች ድጋፍ ከሚያደርጉ በርካታ ማኅበረሰቦች መካከል አንዱ የሚገኝበትን ቀብሪበያን ዛሬ ማለዳ ጎብኝተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ “በጊዜያዊነት የውኃ አቅራቢ ተሽከርካሪዎችን፣ የምግብ፣ የእንስሳት መኖ እና እጅግ አስፈላጊ የሆኑ መድኃኒቶችን አቅርቦት እናሳድጋለን” ሲሉ አስታውቀዋል።
ድርቅ እንዳይከሰት በዘላቂነት ለመከላከል በቆላማ አካባቢዎች የውኃ ክምችትና አጠቃቀምን ለማሻሻል የጀመርናቸውን የአነስተኛ ግድቦች ግንባታ ፕሮጀክቶች እናፋጥናለን ሲሉም አክለዋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n








