በጎንደር ከተማ 314 ሀሰተኛ መታወቂያ ለጠላት ለመስጠት ሲንቀሳቀሱ የተደረሰባቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለፀ

0
1059

ማክሰኞ ጥር 17 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በጎንደር ከተማና ዙሪያ ወረዳ 314 ሀሰተኛ የቀበሌ መታወቂያ ለጠላት አሳልፈው ለመስጠት በድብቅ ሲያጓጉዙ የተገኙ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ዋና ክፍል ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር እየሩስ አስማረ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ከተጠርጣሪዎቹ መካከል አንዱ ጥር 13 ቀን 2014 በተደረገ ክትትል በጎንደር ዙሪያ ወረዳ እንፍራዝ ከተማ 104 ሀሰተኛ መታወቂያዎችን ይዞ ተገኝቷል።

ሌላው ተጠርጣሪ ግለሰብም ጥር 14 ቀን 2014 በጎንደር ከተማ አዘዞ በሚገኘው መናኸሪያ አካባቢ 210 ሀሰተኛ መታወቂዎችን ይዞ መገኘቱን ተናግረዋል።

ከህብረተሰቡ በደረሰን ጥቆማ መሰረት በፀጥታ ሃይሉ በተደረገ ጥብቅ የደህንነት ክትትል ግለሰቦቹ ከነ ሀሰተኛ መታወቂያው እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን አስታውቀዋል።

በአጠቃላይ 314 ሀሰተኛ መታወቂያዎች በግለሰቦቹ እጅ መያዛቸውን አብራርተዋል።

ሀሰተኛ መታወቂያዎቹ በምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ ሽኩራ በተባለ ቀበሌ ሥም የተዘጋጁና ለጠላት ሃይሎች እንዲደርሱ ለማድረግ ታስቦ የነበረ መሆኑን ዋና ኢንስፔክተሯ ተናግረዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በህግ ጥላ ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ጠቁመው፤ ሀሰተኛ መታወቂያዎቹ በባህር ዳር ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ የታተሙ ስለመሆናቸው መረጃዎች እንደሚያመለክቱ ገልጸዋል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here