“የአሜሪካና የኢትዮጽያ የቀደመ ስትራቴጂክ ግንኙነት ወደ ነበረበት ለመመለስ የሚያስችል ስምምነት ላይ ተደርሷል።”፦የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

0
504

ሐሙስ ጥር 18 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የአሜሪካና የኢትዮጽያ የቀደመ ስትራቴጂክ ግንኙነት ወደ ነበረበት ለመመለስ የሚያስችል ስምምነት ላይ መደረሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሰደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫውም ወደ ኢትዮጵያ ከመጣው የአሜሪካ ከፍተኛ የውጭ ጉዳይ ባለስልጣናት ልኡክ ጋር ፍሬያማ ምክክር መደረጉን ገልጸዋል።

በኢትዮጽያ እና በአሜሪካ በኩል የነበረው የመጠራጠር ግንኙነት በተደረገ የሁለትዮሽ ምክክር ወደ ጠራ አቋም ላይ መድረሱንም አክለው አስታውቀዋል።

አሜሪካ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ምክክርን ጨምሮ በጦርነቱ ምክንያት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን ማስታወቋም አምባሳደር ዲና ገልጸዋል።

በተጨማሪም አምባሳደር ዲና በመግለጫቸው፣ ትናንት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተሰጠውን የ27 አምባሳደርሮች ሹመት አንስተውዋል።

ለአምባሳደሮቹ የተሰጠው ሹመት የግለሰሰቦቹ ሙያዊ ብቃትና ክህሎት እንዲሁም አገራዊ ለውጥን መሰረት ያደረገ ነው ሲሉም አብራርተዋል።

ሹመቱ ካለፉት ጊዜያት የተለየና ጥናትን መሰረት ያደረገ ነው ያሉት አምባሳደር ዲና፣ በተጨማሪም ሥራ እና ሰራተኛን በማመጣጠን የተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።

በሹመቱ በውጭ ጉዳይ ሥራ ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉ ግለሰቦች መካተታቸውንም አምባሳደሩ በመግለጫቸው አብራርተዋል።

_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here