አርብ ጥር 20 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበለትን የፌደራል መንግስት 122 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት አፀደቀ።
የ2014 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት የተጨማሪ በጀትና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያ ረቂቅ አዋጅን በ9 ተቃውሞ፣ በ7 ድምፀ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።
ምክር ቤቱ በዛሬው ልዩ ሥብሰባዉ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ረቂቅ አዋጅን መርምሮ በአብላጫ ድምፅ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራቱን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS



