ምክር ቤቱ ለመከላከያ ሠራዊት ተጨማሪ 90 ቢሊዮን ብር በጀት አጸደቀ

0
364

አርብ ጥር 20 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ዛሬ ባካሄደው 3ተኛ ልዩ ሥብሰባው ለመከላከያ ሠራዊት ተጨማሪ የ90 ቢሊዮን ብር በጀት አጽድቋል።

የ2014 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት የተጨማሪ በጀትና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያ ረቂቅ አዋጅን ለምክር ቤቱ ያቀረቡት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጅጌ፣ ተጨማሪ በጀቱ ለሰራዊቱ ስንቅና ትጥቅ የሚውል ይሆናል ብለዋል።

ከመከላከያ ተጨማሪ በጀት ባለፈ ለዕለት ደራሽ ዕርዳታ 8 ቢሊዮን ብር፣ ለመጠባበቂያ በጀት 8 ቢሊዮን ብር፣ ለካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ 7 ቢሊዮን ብር እንዲሁም የታክስ ገቢ ጉድለትን ለማካካስ በበጀት ሽግሽግ ብቻ መሸፈን ባለመቻሉ ለወጪው አሸፋፈን ማስተካከያ 9 ቢሊዮን ብር እንደሚያድስፈልግ ተገልጿል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።

በአጠቃላይ 122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀትና ማስተካከያ ረቂቅ አዋጅ ለምክር ቤቱ ቀርቦ መፅደቁ ታውቋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here