በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ የተመራው የልዑክ ቡድን ከሳውዲ ባለስልጣናት ጋር መመካከሩ ተገለጸ

0
529

አርብ ጥር 20 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የተመራው የልዑክ ቡድን ከሳውዲ አረቢያ የንጉስ ሰልማን የሰብአዊ እርዳታ ማእከል የበላይ ሀላፊ ዶ/ር አብዱላህ አልራቢሀ ጋር በሁለቱ አገራት የጋራ ሰብአዊና የእርዳታ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ሚኒስትሩ ከሳውዲ ልማት ፈንድ ሥራ አስኪያጅ ሱልጣን አልማርሻድ ጋርም ተገናኝተው የተወያዩ ሲሆን፣ በሳውዲ ልማት ፈንድ የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያ የሚያካሄዱትን የልማት ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ያሉበት ሁኔታ በጋራ ገምግመዋል፡፡

በሳውዲ ልማት ፈንድ የገንዘብ ድጋፍ የሚካሄዱ የልማት ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች በመሰረተ ልማት አውታሮች ዝርጋታና ዘላቂ ልማትን ለማምጣት በሚደረገው ጥረት በአገሪቱ ማህበራዊ አገልግሎትና በኢኮኖሚ እድገት ላይ አዎንታ አስተዋጾኦ እንዳለው መግለፃቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በገንዘብ ሚኒስትሩም ሳውዲ አረቢያ በሰብአዊ እርዳታና በኢኮኖሚ ልማት ለምታደርገው ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here