በመዲናዋ ከዛሬ ጀሮ ማስክ ያላደረጉ አሽከርካሪዎች እና ረዳቶች 1 ሺህ ብር እንደሚቀጡና፣ ማስክ ያላደረጉ ተሳፋሪ የሚጭኑም በአንድ ሰው 500 ብር እንደሚቀጡ የትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ

0
455

አርብ ጥር 20 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በከተማዋ የኮቪድ 19 ሥርጭትን ለመግታት በትራንስፖርት ዘርፍ የተቀመጠውን መመሪያ ተግባራዊ በማያደርጉ አሽከርካሪዎች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ቁጥጥር እንደሚደረግ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

የትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት የተሽከርካሪዎችን ንጽህና መጠበቅ፣ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች ማስክ መጠቀም እንዲሁም ማስክ ያላደረጉ ተሳፋሪዎች አገልግሎት እንዳያገኙ ማድረግ እንደሚገባም መመሪያ ተላልፏል፡፡

የኮቪድ ሥርጭት ለመግታት በወጣው መመሪያ መሰረት ማስክ ያላደረጉ አሽከርካሪዎች እና ረዳቶች ከተገኙ ብር 1 ሺህ የሚቀጡ ሲሆን ማስክ ያላደረጉ ተሳፋሪ በሚጭኑበት ወቅት በአንድ ሰው 500 ብር የሚያስቀጣ ይሆናል ተብሏል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ የአዲስ አበባ ትራንስፓርት ቢሮ መግለጫ የሰጠ ሲሆን፣ በመግለጫ ወቅት የትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ይርጋለም ብርሃኔ እንደተናገሩት በትራንስፖርት ዘርፍ የቫይረሱን ርጭት ለመግታት አስገዳጅ መመሪያዎችን በማውጣት ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

ይርጋለም አክለውም በአሁኑ ወቅት በነዋሪዎች ዘንድ የጥንቃቄ መርሆዎች እየተዘነጉ በመምጣቸው የሥርጭት መጠኑ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም የሥርጭት መጠኑ ለመቀነስ ትራንስፖርት በምንገለገልበት ወቅት ማስክ ማድረግና ሌሎች ህጎች አስገዳጅ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

በትራንስፖርት ዘርፍ በከተማዋ የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመግታት የወጣውን መመሪያ በማይተገብሩ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ምክትል ቢሮ ኃላፊው አሳስበዋል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here