ከኢትዮጵያ ተነስቶ አፍሪካን የሚወክል ሚዲያ በምስረታ ላይ መሆኑ ተገለፀ

0
1138

ማክሰኞ የካቲት 1 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ከኢትዮጵያ ተነስቶ አፍሪካን የሚወክል ሚዲያ በምስረታ ላይ መሆኑ ተገለፀ::

“ግሎባል ቴሌቭዥን ኔትዎርክ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ” የመጀመሪያውን ምዕራፍ አጠናቆ በሁለተኛ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ የሚዲያው መስራችና ሥራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ግሩም ጫላ አስታውቋል።

ሚዲያው በአፍሪካ ከመረጃ ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ዘመኑን በሚመጥን የሚዲያ ግብዓት ተደራጅቶ የሚሰራ መሆኑ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ አፍሪካን አንድ በማድረግ ሂደት ያላትን ፋይዳ መነሻ በማድረግ ሚዲያው ከኢትዮጵያ በመነሳት በመላው አፍሪካ የሚሰራ እንደሆነም ግሩም ጫላ ተናግሯል።

ሚዲያው መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገና ለዚህም 5 ሺህ ካሬ የሚገመት መሬት 30 ሚሊዮን ብር የሊዝ ገቢ በማድረግ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መረከባቸውን ጋዜጠኛ ግሩም ገልጿል።

ሚዲያው በመላው አፍሪካ ዘጋቢዎች ይኖሩታል የተባለ ሲሆን፣ በሌሎች የአለም አገራት ኒዮርክ፣ ዋሽንግተን ዲሲ፣ ቤጂንግ እና ለንደን መቀመጫ እንደሚኖረውም መመላከቱን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል።

ሚዲያው ነጻና ገለልተኛ በመሆን የአፍሪካን ገጽታ ለመቀየር በትኩረት ይሰራልም ተብሏል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here