ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሳይንስ እና ትምህርት ዘርፍ የሁለትዮሽ ትብብርን ማጠናከር በሚችሉበት ጉዳይ ዙሪያ መከሩ

0
720

ዕረቡ የካቲት 2 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሳይንስ እና ትምህርት ዘርፍ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ ትብብር እና የሕግ ማዕቀፎችን ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ከሆኑት ኢቭጌኒ ተርኪሂን ጋር ተወያይተዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በሳይንስ እና ትምህርት ዘርፍ እያካሄደች ያለውን የማሻሻያ እቅዶች በተመለከተ ለአምባሳደሩ አብራርተውላቸዋል።

ሩሲያ በርካታ ኢትዮጵያውያንን በተለያዩ ዘርፎች በማሰልጠን ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎችን ስታበረክት የቆየች መሆኑን ያወሱት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፤ ይህም ሩሲያ በኢትዮጵያ የሰለጠነ የሰው ኃይል እንዲኖር ያደረገችው አስተዋጽኦ ዘመን ተሻጋሪ ነው ብለዋል።

የሁለቱ አገራት እውነተኛ የወዳጅነት ምልክት የሆነው የቀድሞው የባሕር ዳር ፖሊ ቴክኒክ ኢንስቲትዩት የአሁኑ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አንዱ ማሳያ ነው ተብሏል።

በኢትዮጵያ ካሉ አንጋፋ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንዱ የሆነው ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በርካታ ልሂቃንን እንዳፈራ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጠቅሰዋል።

በቀጣይም ሁለቱ አገራት ግንኙነታቸውን በማሳደግ የተሻለ ለመሥራት የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውን በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ያገኘኘነው መረጃ ያመላክታል።
____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here