ሰኞ የካቲት 7 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በሱማሌ ክልል በድርቅ ለተፈናቀሉት በርካታ ወገኖቻችን ውሃ በአስቸኳይ ይደርስ ዘንድ ለአንድ ወር በቀን 5 ቦቴ ድጋፍ ጀምረናል ሲሉ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አስታወቁ።
ፕሬዝዳንቷ ዛሬ በቲውተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት እንደገለፁት “በቀብሪ በያ ያየኋቸው ሁሉ በተለይም ሴቶች ጥያቄ አንድ ብቻ ነበር ‘ውሃ’ ነው“ ብለዋል።
ለዘላቂ ጉድጏድ ቁፋሮም ከክልሉ ጋር ተባብረን እንሰራለን ሲሉም ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገልፀዋል።
____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n






