የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የሳይበር ጥቃቶችን የመከላከል አቅሙ ከ96 በመቶ በላይ መድረሱ ተገለጸ

0
743

ሰኞ የካቲት 7 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በተያዘው የበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ውስጥ የሳይበር ደህንነት ጥቃትን የመከላከል አቅሙ ከ96 በመቶ በላይ መድረሱን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ገለጹ።

ዋና ዳይሬክተሩ የስድስት ወር የኤጀንሲውን የሥራ አፈጻጸም አስመልክቶ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

የኤጀንሲው የሳይበር ጥቃቶችን ቅድመ መከላከል፣ ጥቃት የደረሰባቸውን መልሶ ወደ ነበሩበት ሥራ የመመለስ አቅሙ አድጓል ብለዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት ከ3 ሺህ 400 በላይ የሳይበር ጥቃት መኩራ መደረጋቸውንም ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

ባለፉት ጊዜያት በባንኮች፣ በማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት፣ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ በክልል ቢሮዎች፣ የትምህርት ተቋማት፣ የሚዲያ ተቋማትና መሰል ተቋማት የሳይበር ጥቃት ኢላማ ተደርገው እንደነበር ገልጸዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።

ዋና ዳይሬክተሩ በመግለጫቸው አክለውም፣ “በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ሙከራ ተደርጎ የነበረ ቢሆንም ጉዳቱን ማስቀረት ተችሏል” ብለዋል።
____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here