ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ጉባኤ ያላካሄዱ ፓርቲዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንዲያካሂዱ አሳሰበ

0
532

ዕረቡ የካቲት 9 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ጠቅላላ ጉባኤ ያላካሄዱና የሰነድ ማሻሻያ ያላደረጉ ፓርቲዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ጉባኤያቸውን በማከናወን እንዲሁም አስፈላጊ የሰነድ ማሻሻያዎችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በማድረግ እንድታስገቡ ሲል ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳስቧል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዳር 23 ቀን 2014 ከፓርቲዎች ጋር ባደረገው ምክክር በአዋጅ ቁጥር 1162/11 እና በመመሪያ ቁጥር 3/2011 መሠረት ከ6ተኛው አገራዊ ምርጫ መጠናቀቅ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂዱና የሰነድ ማሻሻያ እንዲያደርጉ የተገለፀላቸው ፓርቲዎች፤ የሚጠበቅባቸውን አጠናቀው ባለማቅረባቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተነሳ በአንድ ወር ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን እንዲያከናውኑ እና ለቦርዱ እንዲያስገቡ መወሰኑ በምክክሩ ወቅትም ለፓርቲዎች መገለጹ ይታወሳል።

በዚህም መሰረት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትላንትናው ዕለት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ መወሰኑን ተከትሎ ከሥር ሥማቸው የተዘረዘረ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ በማከናወን እንዲሁም አስፈላጊ የሰነድ ማሻሻያዎችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በማድረግ እንዲያስገቡ ቦርዱ አሳስቧል።

አገራዊ ፓርቲዎቹ:-
1. የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ
2. የኢትዮጵያ ነፃነት ፓርቲ
3. የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ
4. ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ
5. የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ
6. አዲስ ትውልድ ፓርቲ
7. የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት
8. የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር
9. ብልፅግና ፓርቲ
10. የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ
11. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር
12. ኅብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
13. የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ
ክልላዊ ፓርቲዎች
1. የሲዳማ አርነት ንቅናቄ
2. ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ
3. የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ
4. ሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
5. ኅዳሴ ፓርቲ
6. የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
7. የአፋር ሕዝቦች ፍትሐዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ
8. የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ
9. ቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ
10. ዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲ ሉዓላዊነት
11. የአርጎባ ብሔረ ሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
12. የአርጎባ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
13. የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here