“በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳት ትክክለኛ እርምጃ ነው“:- ቱርክ

0
479

በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳት ትክክለኛ እርምጃ ነው ስትል ቱርክ ገለጸች፡፡

የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ መወሰኑን አገሪቱ በበጎ ጎኑ እንደምታየውና እንደምትቀበለው አስታውቋል።

ውሳኔው በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት የሚያስችል ትክክለኛ እርምጃ እንደሆነ ቱርክ እንደምታምንም ተመላክቷል፡፡

በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት የሚደረጉ ሁሉንም ጥረቶች መደገፏን እንደምትቀጥልና ለስኬታማነቱም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ትሰራለች ሲል የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here