ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በሱዳኑ መሪ ላይ የተደረገውን የግድያ ሙከራ አወገዙ

Views: 527

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በሱዳኑ አቻቸው አብደላ ሀምዶክ ላይ ዛሬ የካቲት 30/2012 የተደገረውን የግድያ ሙከራ እንደሚያወግዙ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስታወቁ።

የሱዳን ሕዝብ ሰላሙን ለማስጠበቅ ከፍተኛ ዋጋ ከፍሎ የሚደነቅ እርምጃ ወስዷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ ያሉ ክሥተቶች የሱዳንን መረጋጋትና የለውጥ ጉዞ ሊያደናቅፉ አይገባም ብለዋል።

ኢትዮጵያ በሱዳን አብዮት ማግስት ግጭት እና አለመግባባት መከሰቱን ተከትሎ በአገሪቷ ያሉ የተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖች መግባባት ላይ እንዲደርሱ እና የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም ከፍተኛ ሚና መጫወቷ ይታወሳል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com