የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ለዶ/ር እንግዳ አበበ ሰጠ

0
916

ሐሙስ የካቲት 10 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የማኔጅመንት ቦርድ በየካቲት 9/2014 ባደረገው ሥብሰባ ለመጀመሪያ ጊዜ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ለዶ/ር እንግዳ አበበ ገላን ሰጥቷል፡፡

የሕክምና ኮሌጁ በሥብሰባው የዶ/ር እንግዳ አበበን መረጃዎች ከገመገመ በኋላ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን በዛሬው ዕለት አስታውቋል::

ፕሮፌሰር እንግዳ አበበ ገላን የሕክምና ዲግሪያቸውን (MD) ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ፣ የቀዶ ህክምና ስፔሻሊቲ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቀዶ ህክምና እንዲሁም የሰብ-ስፔሻሊቲ ዲግሪያቸውን በኩላሊት ንቅለ ተከላ ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ያገኙ ሲሆን፤ የተለያዩ አጫጭር የሞያ ሥልጠናዎችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር መከታተላቸውን የሕክምና ኮሌጁ አስታውቋል፡፡

ፕሮፌሰር እንግዳ አበበ ገላን በግላቸውና ከሙያ አጋሮቻቸው ጋር ከ40 በላይ በምርምር የተደገፉ ጥናታዊ ፅሁፎችን በታወቁ አገራዊና አለምዓቀፋዊ መፅሄቶች ላይ ለህትመት አብቅተዋል፡፡

ከነዚህም መካከል 15ቱ ተገምግመው የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ለማግኘት ከሚጠበቅባቸው 40 የህትመት ነጥብ 62 ነጥብ 5 አስመዝግበዋል። በተጨማሪም የተለያዩ ኃላፊነቶችን በመውሰድ በታላቅ ትጋት ለኮሌጁ አገልግሎት የሰጡ ሲሆን በርካታ የማህበረሰብ አገልግሎቶችና የሙያ ነክ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

በቀዶ ህክምና የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው ፕሮፌሰር እንግዳ አበበ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሕክምና ኮሌጅ በሚገኘው የህክምና ትምህርት ቤት ውስጥ የቀዶ ህክምና ትምህርት ክፍል ሀላፊ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here