ኢትዮጵያ ውስጥ በታጣቂ ቡድኖች በሚፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየተፈፀሙ መሆኑ ተገለጸ

0
633

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኢ (ኢሰመጉ) ለአዲስ ማለዳ በላከው መግለጫ እንደገለፀው፣ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሠቶች ኹኔታ ዘግናኝ እና አሳሳቢ በሚባል ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በተጨማሪ የታጠቁ ቡድኖች በኢትዮጵያ በተለያዩ አከባቢዎች ላይ የሚያደርሱት ጥቃት እና የሠብዓዊ መብት ጥሠት በተደጋጋሚ የሚፈፀሙ መሆናቸውን ተከትሎ ጉባኤው እንደሚያሳስበው ከዚህ በፊት በሠጣቸው መግለጫው ላይ የጠቆመ ሲሆን፣ እንደነዚህ ያሉ ተመሳሳይ ጥቃቶች አሁንም ቀጥለዋል ነው ያለው።
በተደጋጋሚ በታጣቂ ኃይሎች በኦሮሚያ ፣አማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ እና ጋምቤላ ክልሎች፣ እንዲሁም በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እየተፈፀሙ ያሉ የሠብዓዊ መብት ጥሠቶች እንደሚያሳስበው ነው ኢሰመጉ የገለጸው።
መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ አሳስቧል። በዓለም አቀፍ ፣በአህጉር አቀፍ እና በአገር አቀፍ ሕጎች መሠረት መንግሥት የዜጎችን በሕይወት የመኖር መብት፣ የአካል ደኅንነት መብት በማስከበር ረገድ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንዲወጣ፣ በታጣቂ ቡድኖች እየተፈፀሙ ያሉ ዕገታዎችን እንዲያስቆም ፣በተመሳሳይ ድርጊቱን የሚፈጽሙ አካላትን በአፋጣኝ ለፍርድ እንዲያቀርብ፣ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በሙሉ ለዚህ ጉዳይ ትኩረት በመስጠት ዘላቂ የሆነ መፍትሔ እንዲያስቀምጡ ጥሪ አቀርባለሁ ሲል ነው ጉባኤው ያሳሰበው።
በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሜ ወረዳ በተጨማሪ የተፈፀመውን ጉዳይ አስመልክቶ መንግሥት በአፋጣኝ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ማቅረቡን ኢሰመጉ ጠይቋል።


ቅጽ 4 ቁጥር 172 የካቲት 12 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here