በጋምቤላ ክልል የእናቶች እና ሕጻናት ጤና ማሻሻያ መረሃ-ግብር ተጀመረ

0
665

በጋምቤላ ክልል በአውሮፓ ኅብረት የገንዘብ ድጋፍ የሚተገበር የእናቶች እና ሕጻናት ጤና ማሻሻያ መረሃ-ግብር በይፋ መጀመሩ ተሠምቷል።
የእናቶች እና ሕጻናት ጤና ማሻሻያው “ለሥርዓተ ፆታ እኩልነት የማኅበራዊ ጤና ቁርጠኝነት” በሚል መረሃ-ግብር በክልሉ ባሉ አራት ወረዳዎች ላይ ፕሮጀክቱ እንደሚተገበር መገለጹ ተመላክቷል።
ዘገባው የሚያመላክተው ከሆነ፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በመድረኩ ላይ ተገኝተው፣ የማኅበረሠብ ጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት አሁን ካለበት ደረጃ ለማሻሻል የሚመለከታቸው መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የጤናን አጀንዳ የጋራ በማድረግ እየሠሩ እንደሚገኙ መግለጻቸውን ነው።
ከዚህም በተጨማሪ፣ የእናቶችንና ሕጻናት ሕመምና ሞት ለመቀነስ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት በየዕድሜያቸው የሚያስፈልጋቸውን የአመጋገብ ሥርዓት እንዲከተሉ በማስተማርና ክትትል በማድረግ የአዕምሮና የአካል ጥንካሬ ብቃት ያለው ቀጣይ የአገር ተስፋ ሰጪ ትውልድ ለማፍራት ኹሉም የድርሻውን ሊያበረክት እንደሚገባ መገለጹም ተዘግቧል።
በተያያዘም፣ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ የሆኑት ኡጁሉ (ዶ/ር)፣ ለሦስት ዓመት ከ268 ሚሊየን ብር በላይ በጀት ተይዞ በሥረዓተ ምግብ ላይ እየተሠራ አንደሆነ እና በቀጣይም ኹሉንም የጤና ዘርፎች ለማሻሻል እየተሠራ እንደሚገኝ መመላከቱን መናገራቸውን ለማወቅ ተችሏል።
በክልሉ ውስጥ ለፕሮጀክቱ ትግበራ ከተለያዩ ወረዳዎች ማለትም ዲማ፣ መንገሺ፣ ኢታንግ እና መኮይ የተጠቀሱ ሲሆን፣ በአካባቢዎቹም 20 ትምህርት ቤቶች፣ 12 ጤና ጣቢያዎች፣ ሦስት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች መለየታቸውምን በዝርዝር ተብራርቷል ነው የተባለው።
ወረዳዎቹ የተመረጡት ችግሩ ጎልቶ ስለሚታይባቸው መሆኑንም መገለፁን ከጋምቤላ ፕሬስ ሴክሬታሪያት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክት ነው የተገለጸው።


ቅጽ 4 ቁጥር 172 የካቲት 12 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here