5ተኛው የ”ኦዳ አዋርድ” ከኦሮምኛ በተጨማሪ የአፋርኛ እና የሲዳመኛ የኪነጥበብ ባለሙያዎች የህይወት ዘመን ተሸላሚ እንደሚሆኑበት ተገለጸ

0
1341

አርብ የካቲት 18 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በዘንድሮው 5ተኛው የ”ኦዳ አዋርድ” ከኦሮምኛ በተጨማሪ በአፋርኛ እና በሲዳምኛ ቋንቋዎች ከፍተኛ የኪነጥበብ ሥራዎችን የሰሩ ባለሙያዎች የህይወት ዘመን ተሸላሚዎች እንደሚሆኑ የኦዳ አዋርድ አዘጋጅ የሆነው በሻቱ ቶለማሪያም መልቲሚዲያ አስታውቋል።

በሻቱ ቶለማሪያም መልቲሚዲያ ከኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ጋር በመተባበር የሚዘጋጀው 5ተኛው ኦዳ አዋርድ የፊታችን የካቲት 29 ቀን 2014 በሸራተን አዲስ ሆቴል ይካሄዳል።

በዕለቱም በሙዚቃ፣ በፊልም እንዲሁም በመፅሀፍ ዘርፍ ከ60 በላይ እጩዎች ቀርበው አሸናፊዎች ተለይተው የሚሸለሙ ይሆናል።

በእጩነት የሚቀርቡት ሥራዎችም ከመስከረም 1 እስከ ጷግሜ 5 2013 ድረስ የተሰሩ የኪነጥበብ ሥራዎች እንደሚሆኑ፤ የበሻቱ ቶለማሪያም መልቲሚዲያ ሥራ አስኪያጅና የ”ኦዳ አዋርድ” አዘጋጅ በሻቱ ቶለማሪያም ገልፃለች።

የዳኝነት ሂደቱ 70 በመቶው በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ እና እውቀት ባላቸው ባለሙያዎች የሚከናወን ሲሆን፤ ቀሪው 30 በመቶ በዳኞቹ የተሻለ ነጥብ ያገኙት ሥራዎች ለመጨረሻ የህዝብ ዳኝነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መላኪያ 8222 ላይ ድምፅ እንዲያገኙ ይደረጋል ተብሏል።

የ2013 የ”ኦዳ አዋርድ” በእጩነት የሚቀርቡ ዘርፎች

1. የአመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ
2. ምርጥ የአመቱ የሙዚቃ አቀናባሪ
3. የአመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም
4. የአመቱ ምርጥ አዲስ ድምፃዊ
5. የአመቱ ምርጥ ዘመናዊ ሙዚቃ
6. የአመቱ ምርጥ የሙዚቃ ጥምረት
7. የአመቱ ምርጥ ሴት ድምፃዊ
8. የአመቱ ምርጥ ቪዲዩ ክሊፕ
9. የአመቱ ምርጥ ፊልም
10. የአመቱ ምርጥ ሴት ተዋናይ
11. የአመቱ ምርጥ ወንድ ተዋናይ
12. የአመቱ ምርጥ ሲኒማቶግራፈር
13. የአመቱ ምርጥ ቪዲዮ ኤዲተር
14. የአመቱ ምርጥ ፊልም ጽሑፍ
15. የአመቱ ምርጥ ደይሬክተር
16. የአመቱ ምርጥ ግጥም መጽሐፍ
17. የአመቱ ምርጥ ልቦለድ መጽሐፍ ሲሆኑ በተጨማሪም አገራዊ አንድነትን ታሳቢ በማድረግ ከኦሮምኛ በተጨማሪ በአፋርኛ እና በሲዳምኛ ቋንቋዎች ከፍተኛ የኪነጥበብ ሥራዎችን የሰሩ ባለሙያዎች የህይወት ዘመን ተሸላሚዎች እንደሚሆኑ አዲስ ማለዳ ከሽልማት አዘጋጆቹ ለማወቅ ችላለች።

በሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ላይም የፌዴራል እና የክልል ሥራ ሀላፊዎች፣ የአገራችን የኪነጥበብ ባለውለታዎች፣ የመገናኛ ብዙሃን ተቆማትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል።

በእዮብ ውብነህ
___
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

 

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here