አርብ የካቲት 18 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በዩክሬን በትምህርት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ከመንቀሳቀሳቸው በፊት በጀርመን በርሊን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዲያሳውቁ ኤምባሲው አሳሰበ፡፡
ኤምባሲው በአገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እና ችግር እንደሚረዳ በመግለፅ፤ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ለደኅንነታቸው ሲባል ከመንቀሣቀሣቸው በፊት በማንኛውም ጊዜ በ+491767269094 የሞባይል ስልክ ቁጥር እና በ [email protected] ኢሜይል አድራሻ በመጠቀም ኤምባሲውን እንዲያገኙ እና እንዲመካከሩ አሳስቧል፡፡
ከትናንት ጀምሮ ሩሲያ በዩክሬን ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄደች መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፤ በአሁነ ሰዓት በአገሪቱ የከፍተኛ ትምህርትን የሚከታተሉ በአጠቃላይ ከ400 እስከ 500 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙ ይገመታል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n




