ፍርድ ቤት በታምራት ነገራ ጉዳይ ተጨማሪ 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቀደ

0
557

የገላን ከተማ ፍርድ ቤት በተራራ ኔትወርክ ዋና አዘጋጅ ታምራት ነገራ ጉዳይ ለፖሊስ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል፡፡
ታምራት ነገራ ባለፈው ሳምንት የካቲት 10/2014 ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረ ሲሆን፣ በወቅቱ ለፖሊስ የ7 ቀን የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ እንደተሠጠበት ይታወሳል፡፡
በዛሬው ዕለት በተሠየመው ችሎት በተመሳሳይ ፖሊስ ምርመራዬን አላጠናቀቅኩም ማለቱን ተከትሎ የጠየቀው ተጨማሪ የ14 ቀን ተፈቅዶለታል፡፡
በጉዳዩ ላይ የታምራት ነገራ ጠበቃ አቶ ገመቹ ጉተማ ጉዳዩ የሽብር ወንጀል ነው ከተባለ ጉዳዩን መመርመር የሚችለው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስለሆነ፤ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ደግሞ ተጠሪነታቸው ለፌዴራሉ በመሆኑ ጉዳዩ ወደ ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መዛወር አለበት ሲሉ ቢከራከሩም ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል፡፡
በተጨማሪም ጠበቃው ለፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄ ቢያቀርቡም ፍርድቤቱ ምላሽ ሳይሰጥ ማለፍን ተራራ ኔትወርክ ነግረውኛል ብሏል፡፡ ችሎት ላይ የጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ቤተሰቦች የፍርዱን ሒደት እንዳይከታተሉ በፖሊስ መከልከላቸው ተገልፃል።
በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ወቅት የታሠረው የተራራ ኔትዎርክ ዋና አዘጋጅ ታምራት ነገራ፣ ያለፉትን 77 ቀናት በኦሮሚያ ክልል ገላን ከተማ በዕሥር ላይ አሳልፏል።


ቅጽ 4 ቁጥር 173 የካቲት 19 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here