የብልፅግና ፓርቲ የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤውን ከመጋቢት 2 እስከ 4 ድረስ ያካሂዳል

0
789

ሰኞ የካቲት 21 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የብልፅግና ፓርቲ የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤውን ከመጋቢት 2 እስከ 4/ 2014 ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።

ብልፅግና ፓርቲ የሚያካሂደውን ጉባኤ አስመልክቶ የፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አደም ፋራህ በሰጡት መግለጫ፤ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ እና ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፉት ጊዜያት ስብሰባ ማካሄዳቸውን ገልጸዋል።

በስብሰባቸውም በተለያዩ ወሣኝ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተው አቅጣጫ ማስቀመጣቸውንም ተናግረዋል።

ፓርቲው ” ከፈተና ወደ ልዕልና ” በሚል መሪ ቃል የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤውን ከመጋቢት 2 እስከ 4/ 2014 በአዲስ አበባ የሚያካሂድ መሆኑንም ያስታወቁት ሃላፊው፤ የፓርቲውን አመራሮች መምረጥ እና ሌሎች ጉዳዮችም በጉባዔው ይከናወናሉ ተብለው እንደሚጠበቁም ተናግረዋል።

የጉባኤው ዓላማም ፓርቲው ያለፈበትን የለውጥ ጉዞ በመገምገም የታዩ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል እና ድክመቶችን ገምግሞ ለማስተካከል መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

ጉባኤው ላይም 1600 አባላት በድምጽ፣ 400 ሰዎች ያለ ድምጽ፣ 41 የተለያዩ አገራት እህት ፓርቲዎች እንዲሁም የአገር ውስጥ ተፎካካሪ ፓርቲዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉም አደም ገልጸዋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here