የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ እስከ መጋቢት 30 ቀን 2014 ድረስ ባለበት እንደሚቀጥል ተገለጸ

0
772

ሰኞ የካቲት 21 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ከየካቲት 19 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2014 ድረስ ከቀላል ጥቁር ናፍታ፣ ከባድ ጥቁር ናፍታና ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የሌሎች የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑ ተገለጸ፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፤ የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋን አስመልክቶ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ በየአመቱ ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ እየወጣ የሚቀርበው የነዳጅ ምርት የአጠቃቀምና የግብይት ሂደት ላይ ሰፊ ችግሮች የሚስተዋሉበት መሆኑን አመልክቷል።

ሚኒስቴሩ ይህን ሁኔታ ለማስተካከል ህብረተሰቡ ምርቱን በከፍተኛ ቁጠባ የመጠቀምና የግል አሽከርካሪዎችም ተሽከርካሪዎቻቸውን በተመጣጠነ አኳሃን በማንቀሳቀስ ብዙሃን ትራንስፖርትን የመጠቀም ልምድ ሊያዳብሩ እንደሚገባ ገልጿል፡፡

በተጨማሪም በዘርፉ የሚታየውን ህገወጥ የነዳጅ ምርት ዝውውርና ኮንትሮባንድ ተግባራት መከላከልና እርምጃ መውሰድ መንግስት ብቻ የሚወጣው ባለመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በነዳጅ ምርት የሚፈፀመው ህገወጥ ተግባራት በመጠቆምና በማጋለጥ በየደረጃው ካለው የፀጥታ አካል ጋር ሊሰራ ይገባል ብሏል፡፡

መንግስት ነባራዊ ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የኢኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎችን በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥል ለማስቻል የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን አስታውቋል፡፡

በቀጣይም በአለም ገበያ የሚኖረው የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደረግ የሚችል መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here