የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ11 ምሑራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ

0
665

ማክሰኞ የካቲት 22 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የካቲት 18 ቀን 2014 ባደረገው ስብሰባ ለ11 ምሑራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታወቀ።

ዩንቨርሲቲው የአስራ አንዱ ምሑራንን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ፤ አግባብነት ባላቸው የትምህርት ክፍሎች ተመርመሮ፣ በየኮሌጆች አካዳሚክ ጉባዔዎች ተፈትሾ፣ አጥጋቢ በሆነ መልኩ በባለሙያ ተገመግሞ በዩኒቨርስቲው ሴኔት ታይቶ እና ይሁንታ አግኝቶ የቀረበለትን የሙሉ ፕሮፌሰርነት መረጃ የተመለከተው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሥራ አመራር ቦርድ መሰጠቱን በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ ላይ አስታውቋል።

በዚህም መሰረት፦
(1) ዶ/ር ቁምላቸው የሺጥላ
(2) ዶ/ር ሽመልስ አሰፋ
(3) ዶ/ር መንግስቱ ለገሰ
(4) ዶ/ር ጉታ ዘነበ
(5) ዶ/ር ፋሲል አሰፋ
(6) ዶ/ር ጥልዬ ፈይሳ
(7) ዶ/ር ብሩክ ላምቢሶ
(8) ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ
(9) ዶ/ር ዘበነ ክፍሌ
(10) ዶ/ር ተረፈ ደገፋ እና
(11) ዶ/ር ንጉሴ ደዬሳን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አፅድቋል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የሚሰጣቸው ምሑራን በመማር ማስተማሩ፣ በጥናትና ምርምር፣ በዩኒቨርስቲ ውስጥ አገልግሎት እንዲሁም በማህበረሰብ አቀፍና ሙያዊ አገልግሎት በዩኒቨርስቲው ሴኔት ሌጅስሌሽን መሰረት የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ ለተወጡ እና ለዓለም የዕውቀት ስርዓት መዳበር ስኬታማ አበርክቶ ላደረጉ መምህራን እና ተመራማሪዎች መሆኑንም ገልጿል፡፡

ዩኒቨርስቲው ማዕረጉ ለተሰጣቸው 11ዱ መምህራን እና ተመራማሪዎች፣ ለትምህርት ክፍሎቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸውና ቤተሰቦቻቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱን አስተላልፏል።
_________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here