ሰኞ የካቲት 28 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቀ ሳቢያ በእንስሳት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል የወንዝ ውሃን በመጠቀም እየተከናወነ ያለው፤ የእንስሳት መኖ የማልማት ሥራ እንስሳትን ለማዳን ወሳኝ ሚና ተጫውቷል ሲሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ አስታወቁ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ፤ በክልሉ እንደ አንድ የድርቅ ጊዜ ምላሽ አካል፣ የወንዝ ውሃን በመጠቀም “የሱዳን ሳር” የተሰኘውን የእንስሳት መኖ የማልማት ሥራ በሥፋት እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
እኚህን ለእንስሳት መኖነት የሚውሉ እጽዋቶችን የማልማቱ ሥራ በተለይም በሸበሌ እና ዳዋ ዞኖች ላይ እየተከናወነ እንደሚገኝ የገለፁት ሙስጠፌ፤ የእንስሳት መኖ ማልማት፤ የእንስሳትን ህይወት ለማዳን ወሳኝ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n




