ሐሙስ መጋቢት 8 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 609 የብሬን ጥይትና ሌሎች ህገ ወጥ ቁሳቁሶችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የወረባቦ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ።
ፖሊስ ፤ በወረባቦ ወረዳ በቀን 05/7/2014 ህገ ወጥ መሳሪያዎችና እቃዎች ጭኖ ከጭፉራ አቅጣጫ ወደ ሃይቅ ዋናውን መንገድ ይዞ ሲመጣ የነበረ “ኮድ 3 B38052 AA ” የሆነ የጭነት አይሱዙ ቢሲቲማ ከተማ ኬላን በመጣስ ለማምለጥ የሞከረ ቢሆንም የጸጥታ ሃይሎች ባደረጉት ክትትል በ02 ቀበሌ ሃራ መገጠያ አካባቢ ከለሊቱ 10:00 አካቢቢ በቁጥጥር ሥር መዋሉን አስረድቷል።
መኪናው በቁጥጥር ሥር በዋለበት ወቅት በመኪናው ውስጥ 39 ካርቶን ጎልዴን ሲጋራ፣ 33 ካርቶን የሺሻ አፕል፣ 305 የክላሽ ጥይት፣ 609 የብሬን ጥይት፣ 10 የቱርክ ጥይት፣ 22 የUNHCR የእርዳታ ኬንዳ እና 11 ብርድልሶች በጸጥታ አካሉ መያዛቸው ተገልጿል።
ህገ ወጥ ጥይቱና ቁሳቁሶቹ በቁጥጥር ሥር ሲውሉ የመኪና አሽከርካሪ የተሰወረ ሲሆን 3 ተጠርጣሪዎችና መኪናው በቁጥጥር ሥር መዋሉም የወረባቦ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4na




