ገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት ስምንት ወራት ከ221 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ

0
405

ገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት ስምንት ወራት ከአገር ውስጥ ታክስ እና ከውጭ ንግድና ቀረጥ ብር 240 ቢሊዮን 338 ሚሊየን 604 ሺሕ 387 ለመሰብሰብ አቅዶ ብር 221 ቢሊዮን 487 ሚሊዮን 562 ሺሕ 425 ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 92.16 በመቶ ማሳካት መቻሉ ተገልጿል።

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አፈፃፀሙ ከ2ዐ13 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወራት አፈጻጸም ጋር ሲነፃፀር የብር 30 ቢሊዮን 192 ሚሊዮን 916 ሺሕ 457 ወይም 15.78 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ጠቁሟል። የተሰበሰበው ገቢ ከአገር ውስጥ ታክስ ብር 131 ቢሊዮን 121 ሚሊዮን 378 ሺሕ 475 ሲሆን፣ ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ ብር 90 ቢሊዮን 366 ሚሊዮን 183 ሺሕ 950 ብር ነው ተብሏል።

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ፣ የገቢዎች ሚኒስትሩ ላቀ አያሌው በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት አራት የተቋሞቹ ቅርንጫፎች ከሥራ ውጭ ሆነው፣ ከኮሮና ወረርሽኝና መሰል ተጨማሪ ችግሮች ውስጥ በመሆን ከመሰብሰቡ አንፃር እጅግ በጣም ጥሩ አፈጻጸም ነው ማለታቸውን ገልጿል።

ሚኒስትሩ ‹‹በበርካታ ተግዳሮቶች ውስጥ ሆነን ይህ መልካም ውጤት የተመዘገበው ምንም ዓይነት ምክንያት ሳያሳብቡ በወቅቱ ግብራቸውን አስታውቀው በሚከፈሉ ግብር ከፋዮቻችን፣ የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮችና ሠራተኞች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ በመሆናቸው ነው።

እንዲሁም አጋር አካላት እና ሕዝባችን እውነተኛ ድጋፍ ያደረጉልን በመሆኑ የተገኘ ውጤት ነው።›› ብለዋል። በቀሪ አራት ወራትም ከዚህ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የተለመደው መልካም ትብብራችሁ እንዳይለየን ሲሉ ሚኒስትሩ ጥሪ ማስተላለፋቸውም ተገልጿል።


ቅጽ 4 ቁጥር 176 መጋቢት 10 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here