ከ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሊትር በላይ ዘይት ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች መሠራጨቱ ተገለፀ

0
700

ሰኞ መጋቢት 12 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ከ1 ሚሊዮን 831 ሺህ 93 ሊትር በላይ ዘይት በኅብረት ሥራ ማህበራት አማካኝነት ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች መሠራጨቱን የከተማው ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኤጀንሲው የግብይት ዳይሬክተር ደብሪቱ ለኢፕድ እንደገለፁት፣ በድምሩ ከ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሊትር በላይ ዘይት ለነዋሪዎቹ ተሠራጭቷል።

ከተሠራጨው ዘይት ውስጥ በመደበኛ ግዢ ለሸማቾች የቀረበው 1 ሚሊዮን 423 ሺህ 283 ሊትር ዘይት ነው ብለዋል።

በኅብረተሰቡ ጥቆማ በሕገ ወጥ መንገድ ከተያዙ ነጋዴዎች ለኅብረት ሥራ ማኅበራት እንዲያከፋፍሉት የተሰጠ 162 ሺህ 989 ሊትር ዘይት በተጨማሪነት መከፋፈሉም ተገልጿል።

በመዲናዋ ከሚገኙት 148 መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበራት መካከል 133 ያህሉ ዘይት እያሠራጩ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

ሆኖም በዘይት ሥርጭት ረገድ መንግሥት ከፍተኛ ወጪ አውጥቶ የሚገዛው የድጎማ ዘይት በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶ በዝቅተኛ ኑሮ ውስጥ ላሉና ኩፖን ላላቸው ሰዎች እየተከፋፈለ ነው የሚገኘው ተብሏል።

ይህም በራሱ የገበያውን ሁኔታ የሚያረጋጋ መሆኑ ተገልጿል።

የዘይት አቅርቦት እጥረትን ለመፍታት አገር በቀል ኹለት ፋብሪካዎች በከፍተኛ ደረጃ እያመረቱ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን፤ ከኹለቱ ዘይት አምራች ፋብሪካዎች ጋርም የአቅርቦት ውል መፈፀሙ ተገልጿል።
_________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here