የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ ልዑክ ጅግጅጋ ገባ

0
845

ሰኞ መጋቢት 12 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ ልዑክ ሶማሌ ጅግጅጋ ክልል ገብቷል፡፡

ለልዑኩ የሶማሌ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አብዲራህማን አህመድ ሀሰንና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በገራድ ዊልዋል አየር ማረፊያ አቀባበል አድርገዋል።

በኢትዮጵያ የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ዶክተር ካትሪን ሶዚ ከተመድ የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) የኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ቱርሃን ሳሌህ ጋር በመሆን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ዑመር ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የልዑኩ ቡድኑ ጉብኝት ዓላማም በድርቅ ሁኔታና በማህበረሰቡ ልማት ዙሪያ ያሉ ችግሮችን ለመወያየትና ለመፍታት እንደሆነ ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here