ማክሰኞ መጋቢት 13 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ ካካሄዱ በኃላ፤ የጠቅላላ ጉባኤውን ቃለጉባኤ፣ ማሻሻያ ተደርጎበት በጠቅላላ ጉባኤ የፀደቀውን መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም ሌሎች ማሻሻያ የተደረገባቸውን ሰነዶች እና ሪፖርቶች በ15 ቀናት ውስጥ እንዲያስገቡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ።
በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና አዋጁን ለማስፈፀም ቦርዱ ባወጣው መመሪያ ቁጥር 3/2012 መሠረት ፓርቲዎች በመተዳደሪያ ደንባቸው ላይ ሕጉ በሚያዘው መሰረት ማስተካከያዎችን በማድረግ እንዲያቀርቡ መደንገጉን ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n



