አምስት ከባድ የብሬን ጦር መሳሪያዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ

0
1458

ማክሰኞ መጋቢት 13 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) አምስት ከባድ የብሬን ጦር መሳሪያዎችን ከደሴ ወደ ምስራቅ ሐረርጌ ዞን በሕገወጥ መንገድ ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ ከነ ጦር መሳሪያው በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ።

ግለሰቡ የተያዘው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል እንደሆነ ተነግሯል።

መነሻውን አማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ ያደረገ ሕገወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪ ግለሰብ ሰሌዳ ቁጥሩ አአ ኮድ2 B23782 በሆነ ላንድ ክሩዘር ተሽከርካሪ ላይ አምስት ከባድ ብሬን በድብቅ በመጫን መዳረሻውን ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን በማድረግ በመጓዝ ላይ እያለ በቁጥጥር ሥር እንዲውል ተደርጓል።

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የመረጃ ኦፊሰሮች በግለሰቡ ላይ ከመነሻው ክትትል በማድረግ፤ አዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 በተለምዶ ካራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲደርስ ለአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ጥቆማ በመስጠት ከነጦር መሳሪያው እጅ ከፍንጅ መያዙን ኢዜአ ዘግቧል።
_________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here