ማክሰኞ መጋቢት 13 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ከሰሞኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለመጋቢት 17 እና 18/2014 ጠቅላላ ጉባኤ እንደተጠራ ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያ በተለያዩ ግለሠቦች አማካይነት እየተሠራጨ ያለዉ ወሬ ከምክር ቤቱ ሥራ አስፈፃሚዎች እና ፕሬዝደንቱ ዕዉቅና ዉጪ ነዉ ሲል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ።
ምክር ቤቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ይህ የጉባኤ ጥሪ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ ውጭ አገር ከመሆናቸው በተጨማሪ ሌሎችም የዑለማ ምክር ቤት ሥራ አስፈፃሚ አመራሮች የማያውቁት ህገ ወጥ ሲሆን፤ የተጠራዉም ራሱን ”የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የጠቅላላ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ” እያለ በሚጠራ ማንነቱ በማይታወቅ ህገወጥ አካል መሆኑንም ገልጿል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4




