የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ከፌደራል እና ከክልል የጤና ተቋማት ጋር በቅንጅት በመሰራቱ በሰራዊቱ የግዳጅ አፈጻጸም ላይ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡ ተገለፀ

0
1210

ማክሰኞ መጋቢት 13 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ከፌደራል እና ከክልል የጤና ተቋማት ጋር በቅንጅት በመሰራቱ በሰራዊቱ የግዳጅ አፈጻጸም ላይ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ገለፁ።

የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ በሕግ ማስከበርና ህልውና እንዲሁም ለህብረ ብሔራዊ አንድነት ዘመቻ ስኬታማ የግዳጅ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አባላቶቹ ባዘጋጀው የእውቅና እና የሽልማት አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እና ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮች ተገኝተዋል።

በሽልማት እና የእውቅና አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ አመራሮችና ባለሙያዎች በእልህ እና በቁጭት በአነስተኛ የሰው ሃይል ቀን ከሌሊት ተግተው በመስራታቸው መከላከያ ሰራዊታችን ላስመዘገበው ድል ከፍተኛ አስዋጽኦ አበርክተዋል ብለዋል።

የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ከጤና ሚኒስቴር እና መሰል የዘርፉ ተቋማት ጋር በትብብር መሰራቱ ሰራዊቱ በጀግንነት ተዋግቶ እንዲያሸንፍ ከማስቻሉም በላይ የሰራዊቱን ሞራል በሚገነባ መልኩ ውጤታማ ሥራዎች መሰራታቸውን የጠቆሙት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ በሕግ ማስከበርና ህልውና እንዲሁም ለህብረ ብሔራዊ አንድነት ዘመቻ ለተመዘገበው ውጤት ሁሉንም ባለድርሻ አመስግነዋል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይም የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተና ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ ባደረጉት ንግግር፤ በአገራችን ላይ የህልውና አደጋ ተከስቶ በነበረበት ወቅት ዋና መምሪያው ያለውን ውስን የሰው ሃብት በመጠቀም በውጊያው የተሳካ የጤና አገልግሎት ድጋፍ በተቀላጠፈ መንገድ መስጠት መቻሉን ገልጸዋል።

የእውቅና እና የማእረግ እድገት ከተሰጣቸው የዋና መምሪያው አባላት መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት ሽልማቱ ለበለጠ ሥራ እና ሃላፊነት እንደሚያነሳሳቸው መናገራቸውን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመለክታል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here