ዕረቡ መጋቢት 14 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚገቡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እንዲያስተካክሉ የተሰጠው ጊዜ ትላንት መጠናቀቁን ተከትሎ፤ የትምህርት ሚኒስቴር የማስተካከያ ጊዜው ለተጨማሪ ቀናት መራዘሙን አስታወቀ።
በ2013 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ባስመዘገቡት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችላቸው ተማሪዎች ከዚህ ቅደም የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዳቸው ይታወቃል።
ስለሆነም ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን በመግለፅ፤ የሚከተሉትን መረጃዎች እንዲመለከቱ ጠይቋል።
1ኛ. የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ መጋቢት 19 ቀን 2014 ድረስ በ http://Portal.neaea.gov.et በመግባት እንዲያስተካክሉ ጠይቋል።
ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማያስተናግድ መሆኑንም ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
2ኛ. በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላቸው የሚያመለክቱ ተማሪዎች መረጃቸውን እስከ መጋቢት 19 ቀን 2014 ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንዲልኩ በማሳሰብ፤ በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።
_________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n



