ሐሙስ መጋቢት 15 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ተኛ ዙር 1ኛ ዓመት 2ተኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።
በጉባዔው የስድስት ወር የሥራ አፈጻጸም ይገመገማል፤ የስድሰተኛው አንደኛ መደበኛ ጉባዔን ቃለ ጉባዔን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
የበጀት ዓመቱን የስድስት ወር የመልካም አሥተዳደርና የልማት እቅድ የሥራ አፈጻጸም ይገመግማልም። ጉባዔው በሚኖረው ቆይታ የቋሚ ሰብሳቢዎችን ጨምሮ ልዩ ልዩ ሹመቶችን እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል ሲል አሚኮ ዘግቧል።
ጉባዔው ዛሬ እና ነገ በክልሉ ምክር ቤት እንደሚደረግም ታውቋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n






