አዲስ አበባ በአፍሪካ ለኑሮ ውዷ ከተማ በመሆን በቀዳሚነት ተቀመጠች

0
1043

ሰኞ መጋቢት 19 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) አዲስ አበባ በአፍሪካ ከሚገኙና ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ካለባቸው 15 ከተሞች መካከል በቀዳሚነት መቀመጧን ቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ የተባለ ድህረገጽ ይዞት በወጣው መረጃ አስታውቋል።

ቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ የኑሮ ውድነት ደረጃውን በአገራቱ ያለውን የምግብ፣ አልባሳት፣ መዝናኛ፣ የጤና አጠባበቅና መሰል መሠረታዊ ፍላጎቶች አማካይ ወጪዎችን በማነፃፀር ማውጣቱን አስታውቋል።

በዚህም ድህረገጹ ባወጣው አሃዛዊ የኑሮ ውድነት መለኪያ ነጥብ መሰረት አዲስ አበባ በ58 ነጥብ 92 በአንደኛ ደረጃ ተቀምጣለች።

በኹለተኛ እና በሦስተኛ ደረጃ የተቀመጡት የኮትዲቯሯ አቢጃን እና የዚምባቡዌዋ ሀራሬ ከተሞች ሲሆኑ 55 ነጥብ 73 እና 52 ነጥብ 33 በቅድመ ተከተል የኑሮ ውድነት መለኪያ ነጥብ ተሰጥቷቸዋል።

በዝርዝሩ የኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ በ38 ነጥብ 51 እንዲሁም፤ የሞሮኮ ዋና ከተማ ራባት 37 ነጥብ 95 የኑሮ ውድነት ነጥብ በመያዝ በ14ተኛ እና በ15ተኛነት ተቀምጠዋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here