ሐሙስ መጋቢት 22 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የሚገኘው የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ቡድን በሳምንት ከ1 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች በነጻ ስልክ የማስደወል አገልግሎት በመስጠት ቤተሰቦቻቸውን ማናገር እንዲችሉ እያገዘ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ኮሚቴው ከዚህ ቀደም እ.ኤ.አ ከጥር 2021 እስከ ጥር 2022 ባለው ጊዜ ውስጥ በትግራይ ክልል ከቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸው ለተነጣጠሉ 41 ሺህ 326 ሰዎች ነጻ የስልክ ማስደወል አገልግሎት መስጠቱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n




