“ረመዳን ጾም የመተዛዘን፣ የመረዳዳት እና የመከባበር ወቅት ነው”:-ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ

0
529
ሐሙስ መጋቢት 22 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ)የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ 1443ኛውን የረመዳን ጾም አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፕሬዚዳንቱ በመልዕክታቸውም፤ ረመዳን ጾም የመተዛዘን፣ የመረዳዳት እና የመከባበር ወቅት ነው ብለዋል።
በአገራችን በአማራ እና አፋር በጦርነት የተጎዱትን፣ በወለጋ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉትን እና በተለያዩ የአገራችን አካባቢ በድርቅ የተጎዱትን ወገኖች አለንላችሁ ልንላቸው፤ እንባቸውን ልንጠርግላቸው ይገባል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።
ፆሙ የጨረቃን መውጣት ተከትሎ በቀጣይ ቅዳሜ ወይም እሑድ ሊጀምር እንደሚችልም ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here