በመዲናዋ እምቢልታ ሆቴል አካባቢ በአንድ አልኮል መጠጥ መጋዘንና መሸጫ ሱቅ ላይ የእሳት አደጋ ደረሰ

0
1168

አርብ መጋቢት 23 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 እምቢልታ ሆቴል አካባቢ በእንድ አልኮል መጠጥ መጋዘንና መሸጫ ሱቅ ላይ የእሳት አደጋ መድረሱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

አደጋው ዛሬ ጠዋት 2 ሰዓት አካባቢ የደረሰ ሲሆን፤ በአደጋውም የ200 ሺህ ብር ግምት ያለው ንብረት ሲወድም 30 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን መቻሉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለኢዜአ ገልጸዋል።

አደጋው በሰው ላይ አንድ ቀላልና አንድ ከባድ አደጋ ያደረሰ ሲሆን፤ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም ለህክምና ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል መላካቸውን ጨምረው ገልጸዋል።

እሳቱን ለማጥፋት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን 21 ሰራተኞች እና 3 መኪኖች በመጠቀም ወደ ሌላ ቦታ ተዛምቶ ከዚህ የከፋ አደጋ እንዳያደርስ መቆጣጠር መቻሉን ተጠቁመዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ በኤሌክትሪክ ንክኪ ምክንያት መሆኑንም የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ጨምረው ገልጸዋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here