ሰኞ መጋቢት 26 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) “ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ሊፈርስ ነው” በሚል የሚሰራጨው መረጃ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው ሲል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት አስታወቀ።
ዩኒቨርሲቲው ካሉት ኮሌጆች መካከል አንዱና ግንባር ቀደሙ የያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት መሆኑንም አስታውሷል።
ሆኖም አንዳንድ አካላት በተለያዩ የሚዲያ ገፆች ላይ “ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤቱ ሊፈርስ ነው” የሚል የተሳሳተ መረጃዎችን በተደጋጋሚ በማሳራጨት በሕብረተሰቡና በተማሪዎች ላይ ውዥብር ለመፍጠር ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
ነገር ግን በምህርት ቤቱ በኩል ምንም የተፈጠረም ሆነ የተለየ ነገር አለመኖሩን ያሳወቀው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ ሕብረተሰበ በተደጋጋሚ የበሬ ወለደ መረጃ የሚያሰራጩ አካላትን በማጋለጥ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም በበኩሉ፤ አንዳንድ ወገኖች “አንጋፋዉ ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ሊፈርስ ነው” በሚል የሚያሰራጩት መረጃ የተሳሳተ ነው ሲል በትላንትናው ዕለት መግለጹ ይታወሳል፡፡
____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n




