ሰኞ መጋቢት 26 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ቻይና ለኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢዩዋን አስታወቁ።
አምባሳደሩ በአማራ፣ ሲዳማ እና ደቡብ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የኢንዱስትሪ መንደሮችን መጋቢት ወር ላይ መጎብኘታቸውን በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ አስታውቋል፡፡
አምባሳደሩ በጉብኝታቸውም የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለኹለቱም አገራት ሰፊ የሥራ ዕድል እና ዘርፈ-ብዙ ጥቅሞችን በመፍጠር ጉልህ ሚና የሚጫወት እንደሆነ መረዳታቸውን ገልፀዋል።
____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n





