ኢትዮጵያን በኤክስፖ 2020 ዱባይ ያስተዋወቀችዉ ድንቅነሽ (ሉሲ) ወደ አገሯ ተመለሰች

0
636

ዕረቡ መጋቢት 28 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ባለፉት ስድስት ወራት እ.ኤ.አ ከኦክቶበር 2021 እስከ ማርች 2022 በኤክስፖ 2020 ዱባይ በኢትዮጵያ አልፍኝ (ፕቪሊየን) ለዕይታ በመቅረብ ብዙ ጎብኚዎችን የሳበችዉና አገራችን የሰዉ ልጅ መገኛ መሆኗን ያስተዋወቀችዉ ድንቅነሽ ወይም ሉሲ በትላንትናው ዕለት መጋቢት 27 ቀን 2014 ወደ እናት አገሯ ተመልሳለች።

በሽኝት ፕሮግራሙ በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ቆንስል ጄኔራል ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የቆንስላ ጄነራል ጽ/ቤቱ ዲፕሎማቶችና ሰራተኞች የዳያስፖራ አባላት እና የኮሚኒቲ ማህበር ጽ/ቤት ተወካዮች ተገኝተዋል።

በዱባይ ሲካሄድ በቆየዉ ኤክስፖ 2020 ዱባይ ኢትዮጵያን የሚያስተዋዉቁ የተለያዩ የአገራችን ታሪካዊ ቦታዎች፣ አልባሳትና ምርቶች በአዉደ ርዕዩ የቀረቡ ሲሆን፤ በተለይ ኢትዮጵያ የሰዉ ዘር መገኛ መሆኗን ለዓለም ያስተዋወቀችዉ ድንቅነሽ ወይም ሉሲ ከፍተኛ ቁጥር ባለዉ ህዝብ ተጎብኝታለች።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስን ጨምሮ የተለያዪ አገራት ጎብኚዎች የሰዉ ዘር መሠረት የሆነችዉን ሉሲን በአካል በማየታቸዉ ልዩ ደስታ እንደፈጠረባቸዉ እና ኢትዮጵያ የሰዉ ልጅ ዘር መገኛ ጥንታዊ አገር መሆኗን መገንዘባቸዉን መግለፃቸውን በዱባይ እና በሰሜን ኤምሬቶች ከሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ድንቅነሽ ወይም ሉሲ ለአገራችን የቱሪስት መስህብ እና አዎንታዊ ገጽታ በመሆን ከፍተኛ ድርሻ አበርክታለች።

_________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here