ማክሰኞ ሚያዝያ 4 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በአፋር ክልል ሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ በትላንትናው ዕለት በድንገት በተከሰተ የእሳት ቃጠሎ በግምት ከ160 በላይ የሚጠጉ ሱቆች እና መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውን የወረዳው አስተዳድር ገለፁ።
የሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ አስተዳድር ሀሰን ሀንዲ ለአፋር ብዙሀን መገናኛ ድርጅት በስልክ እንደገለፁት የእሳት ቃጠሎ አደጋው የደረሰው ትናንት ወደ 10 :00 ሰዓት አካባቢ በድንገት ከቢንዝል መሸጫ ቤት በተነሳ መሆኑን ጠቁመዋል።
በደረሰው ድንገተኛ የቃጠሎ አደጋም ወደፊት የሚጣራ ሁኖ፤ በግምት ግን ከ80 በላይ መኖሪያ ቤቶች እንደዚሁም ወደ 80 ሊጠጋ የሚችል የተለያዩ የንግድ ሱቆች በእሳት አደጋው የወደሙ ሲሆን በሰው ህይወት ላይ የደረሰ አደጋ ግን የለም ብለዋል።
በአካባቢው ከነበረው ከፍተኛ ንፋስ መኖሩ የተነሳ እና የውሀ እጥረት በመኖሩ ቃጠሎው በፍጥነት በመባባሱ ምክንያትም እሳቱን ለመቆጣጠር ባለመቻሉ ከፍተኛ ውድመት ተከስቷል ሲሉ የወረዳው አስተዳደር አስታውቀዋል።
ስለሆነም በቅድሚያ እሳቱን ማጥፋት እና ተጎጂዎቹ አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
የወረዳው አስተዳደር አክለውም፤ በብዛት የቢንዚል ሽያጭ ከሚከናወንበት ቦታ በቀላሉ የእሳት አደጋ እየተፈጠረ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቂ ሊደረግ ይገባል ሲሉ ማሳሰባቸውን የአፋር መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡
_____________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n





