ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ለተፈናቃሉ ወገኖች በዓል መዋያ የሚሆን ከ800 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ ድጋፍ አደረጉ

0
982

ማክሰኞ ሚያዝያ 11 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ በመጠለያ ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ለበዓል መዋያ ከ870 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ የእርድ ከብቶችን ድጋፍ አድርገዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖችና ከትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት፤ ከዚህ ቀደም ድጋፍ ለማድረግ በመጡበት ጊዜ ዳግም ተመልሰው የቻሉትን እገዛ ለማድረግ ቃል በገቡት መሰረት ለኹለቱም እምነት ተከታዮች የበዓል መዋያ የሚሆኑ የእርድ ከብቶችን ይዘው መምጣታቸውን ገልጸዋል።

የአካባቢው ማህበረሰብ በጦርነቱ አቅሙ በመዳከሙ ብዙ ማገዝ ባይችልም የስደትን አስከፊነት በተግባር ስለሚረዳ በመፈናቀላችሁ ሀዘኑ ከፍ ያለ ነው ያሉት ሊቀ ጳጳሱ፤ አገራችን በፈተና ወድቃ፣ የዜጎች መፈናቀል እና ሰቆቃ እንዲያበቃ እና መልካም ጊዜ እንዲመጣ ኹሉ በየእምነቱ ጸንቶ መጸለይና ይህን የፈተና ጊዜ ማለፍ የሚቻልበትን በጎ ሥራ ማከናወን እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ተፈናቃዮቹ በበኩላቸው፤ በቤተ ክርስቲያኗና በእሳቸው በኩል እየተደረገላቸው ስላለው ድጋፍ ምስጋናን አቅርበዋል፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን ከ34 ሺህ በላይ ስደተኞች እንደሚገኙ የዞኑ ምግብ ዋስትናና አደጋ መከላከል ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here