ለአንዳንድ ቤተሰቦች ልጅ መውለድ ተፈጥሯዊ ሲሆን ለሌሎች ደግሞ በጣም ፈታኝ ተሞክሮ ይሆናል። ከፍ ያለ የእናቶች ዕድሜ፣ ተደጋጋሚ እና ያልተሳካ የመካንነት ህክምና IVF አጋጣሚ፣ ተደጋጋሚ የፅንስ መጨንገፍ፣ ከባድ የወንዶች መካንነት፣ የእንቁላል ክምችት መቀነስ፣ የበሽታ መከላከል ችግሮች እና የመሳሰሉት በታገዘ የእርግዝና ሂደት ላይ እንኳን ተግዳሮቶችን ሊፈጥሩ ይችላሉ።
በቱርክ አቺባደም ሄልዝኬር ግሩፕ የእርግዝና ከፍተኛ ሀኪም የሆኑት ፕሮፌሰር ቼም ፊቺቺዮግሉ የተወሳሰቡ የመካንነት ጉዳዮችን ከ30 ዓመታት በላይ ሲያክሙ ቆይተዋል። “በ IVF ላይ የሚሰራ እያንዳንዱ ከፍተኛ ባለሙያ በእድሜ በአንጻራዊነት ወጣት ታካሚዎችን ይመርጣል፡፡ የዚህም ምክንያት የህክምናው የስኬት መጠን በዝቅተኛ ዕድሜ ክልል ባሉት ላይ በአንጻራዊነት ከፍ ያለ ስለሆነ ነው፡፡ ነገር ግን የእንቁላል ክምችት መቀነስ፣ የእናቶች ዕድሜ ከፍ ማለት ወይም ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ እና ያልተሳካ የ IVF አጋጣሚ ያላቸውን ታካሚዎች ማገዝ በግሌ የበለጠ እርካታ ይሰጠኛል ” ሲል ጠቁመዋል።
ፕሮፌሰር ፊቺቺዮግሉ በቤልጂየም፣ ዩናየትድ ከኪንገግደመም እና ዩናይትድ ሰቴትስ ውስጥ ከሥነ ተዋልዶ ሕክምና እና መካንነት ቀዶ ጥገና ጋር የተያያዙ የትምህርት ፕሮግራሞችን ተከታትለው አጠናቅቀዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በህክምና ቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ መዳረሻ በሆነችው በቱርክ ውስጥ ይሰራሉ፡፡ ውጤታማ የስራ ህይወቱ በቱርክ፣ ቡልጋሪያ፣ ሮማኒያ፣ ስዊዘርላንድ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ሆላንድ፣ አሜሪካ፣ ዩናይትደድ ኪንግደም፣ ኡዝቤኪስታን፣ ካዛኪስታን፣ ሞልዶቫ እና ሌሎችም ሀገሮች አሁን ደስተኛ ለሆኑ ጥንዶች ከ30,000 በላይ ሕፃናት ልጀች እንዲያገኙ አስችሏለል። በዕለት ተዕለት ሥራው ውስጥ የIVF ህክምና ተከታታየቹ በአማካይ ወደ 30 ዓመት ገደማ ሲሆኑ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የታካሚዎቹ አማካይ ዕድሜ በየጊዜው እየጨመረ መጥቷል፡፡ የዕድሜ መግፋት አንዳንድ የተወሳሰቡ እና የልዩ ባለሞያዎች ችሎታ እና ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ችግሮች ሊያመጣ ይችላል። ‘የተወሳሰቡ’ ጉዳዮች ያሉባቸው ጥንዶች ሁሉ የሚታመኑትን ዶክተር እና ክሊኒኮች በሚመርጡበት ጊዜ ከግምት ሊያስገቧቸው የሚገቡትን ሦስት ዋና ዋና ለስኬታማ የመካንነት ህክምና የሚያስፈልጉ ቁልፍ ነገሮችን ፕሮፌሰር ቼም ፊቺቺዮግሉ ጠቁመዋል።
በቱርክ ካሉ ባለሞያዎቻችን ነፃ የህክምና አስተያየት ለማግኘት አሁን ያግኙን
https://acibademinternational.com/
የላቀ የላብራቶሪ አገልግሎት
ስኬታማ የሆነ የወሊድ ህክምና የከፍተኛ ባለሙያ ችሎታ እና የቡድን ስራን ይጠይቃል፡፡ የሕክምና ፕሮቶኮሎችን የሚወስነው፣ በሽተኞቹን የሚከታተው እና ለእርግዝና አስፈላጊ የሆኑትን የኦክሳይቶችን (oocytes) ሴሎች የመመለስ ስራ የሚሰራው የእርግዝና ሐኪሙ ነው፡፡ ሆኖም ፅንሱ ከመተላለፉ በፊት የተመረጠውን እንቁላል እና የወንድ ዘር ሴሎችን ለማዳቀል፣ ፅንሱን ለማደግ እና ለመንከባከብ እንዲሁም ሁሉንም አስፈላጊ የላብራቶሪ ሂደቶችን ለማከናወን ሀላፊነት የሚሰጠው ለፅንሱ ባለሙያ (embryologist) ነው። ፕሮፌሰር ቼም ፊቺቺዮግሉ የፅንሱን ላብራቶሪ በ IVF ከሐኪሙ እውቀት ጋር ለመጨረሻው ውጤት እጅግ አስፈላጊ ሂደቶች ወቅት እንደ ‘የመድሃኒት ማእድ ቤት’ ሆኖ የሚገለግል በማለት ይገልፀዋል፡፡ “እነዚህን ሁሉ ሂደቶች የሚቆጣጠሩ፣ ህክምናውን ለግለሰቡ እንደሚሆኑ ተደርገው የሚያበጁ እና በቅርብ የሚከታተሉት የፅንስ ባለሙያዎች ብቃት እና ቴክኖሎጂ ለስኬት ቁልፍ ነጥብ ነው” ብሏል።
ለምሳሌ በአቺባደም የፅንስ ላብራቶሪ በዘርፉ እጅግ በጣም ልዩ የሆኑ ስፔሻሊስቶችን፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታጠቁ እና ከአለም ዙሪያ ካሉ የተወሳሰቡ የመካንነት ጉዳዮች ላይ በመደበኛነት የሚሰሩ ባለሙያዎችን ይቀጥራል። በዘርፉ ለላቀ ስኬት አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ ሁሉም የቅርብ ጊዜ መሳሪያዎች አሏቸው። ፅንሶችን በፅንስ ማጎልበት እና በ embryoscope ቁጥጥር ማድረግ ይቻላል፡፡. ይህ ፅንሱን ለማዳበር በጣም ጥሩ ሁኔታዎችን የሚፈጥር ኢንኩቤተር ሲሆን ፅንሶቹ ለዚሁ አግልግሎት አብሮ በተሰራ ካሜራ ይታያሉ፡፡ ይህም ጽንሱ ወደ መደበኛ ክፍል ሁኔታዎች መውጣትና መግባት አንዳያስፈልገው ያደርጋል። የማይክሮማኒፑሌተር መሳሪያ (Micromanipulator) ለፍጹም የቀረበ ትክክለኛነትን ለሚፈልጉ ቴክኒኮች ጥቅም ላይ እየዋለ ነው፡- ለምሳሌ የታገዘ መፈልፈያ (AHA)፣ ቅድመ-ኢምፕላንት ጄኔቲክ ምርመራ (PGD) ወይም የወንድ ዘር ማስገባት intracytoplasmic sperm injection (ICSI) የመሳሰሉትን ይይዛል፡:፡ እነዚህ ሁሉ የእርግዝና ደረጃዎችን የሚያሻሽሉ መሳሪያዎች ናቸው፡፡
ግለሰብ ማዕከል ያደረገ አቀራረብ እና ህክምና
“እያንዳንዱ ታካሚ የራሱ የሆነ ጉዞ አለው። እያንዳንዱ የወሊድ ጉዳይ የራሱ ፈተናዎች አሉት፡፡ ስለዚህም ምንም እንኳን ተመሳሳይ ዕድሜ ቢሆኑም የአንድ ሰው የሕክምና ፕሮቶኮል ብዙውን ጊዜ ከሌላው በጣም የተለየ ነው ይላሉ ፕሮፌሰር ቼም ፊቺቺዮግሉ ። ከምርመራው አንስቶ እስከ ህክምናው ድረስ የግለሰቡን ሁኔታ ከግምት ማስገባት ወሳኝ ጠቀሜታ የሚኖረው ለዚህም ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ወደ 20% የሚጠጉ ታካሚዎች ‘ያልታወቀ መካንነት’ የሚባሉት ችግሮች አሏቸው። “ይህ ማለት መካንነትን የሚያመጣ ምንም ምክንያት ማግኘት አልቻልንም ማለት ነው” ሲሉ ፕሮፌሰር ፊቺቺዮግሉ ያብራራሉ። እንዲህ ላሉት ታካሚዎች አሁንም የተለያዩ አማራጮች አሉ፡፡ “ሴቲቱ ከ 35 እስከ 36 ዓመት ዕድሜ በታች ከሆነች ፣ ጥሩ የእንቁላል ክምችት ካላት እና የትዳር ጓደኛዋ ጥሩ የወንድ የዘር ህዋስ (sperm count) ካለው ታዲያ በማህፀን ውስጥ የማዳቀል ስራ intrauterine insemination (IUI) እንዲመርጡ እንመክራቸዋለን። ነገር ግን የሴቷ ዕድሜ ከ 36 ዓመት በላይ ከሆነ ፣ የመካንነት ጊዜ ከ 6 ዓመት በላይ ከሆነ እና የወንድ የዘር ህዋሱ ዝቅተኛ ከሆነ ወዲያውኑ የመካንነት ህክምና (IVF) ሂደትን እንመክራለን፡፡
አንዳንድ ጥንዶች ወደ ተፈጥሯዊነት የቀረበን የእርግዝ ሕክምናን ይመርጣሉ፡፡ ይህም አጭር ፕሮቶኮሎች እና አነስተኛ ማነቃቂያ የሚጠይቅ ነው። እንደ ፕሮፌሰር ፊቺቺዮግሉ ገለጻ አጠር ያለ ጊዜ የሚወስድ፣ ዝቅተኛ ክፍያ የሚጠይቅ፣ ጥቂት የወሊድ መድሃኒቶችን መውሰድ የሚበቃው መሆኑ እና ሌሎች እንዲህ ያሉ አንዳንድ ጥቅሞችን ይሰጣል። ነገር ግን በልማዳዊው የመካንነት ህክምና IVF ብዙ oocytes ሴሎች ስለሚፈጠሩ ፅንሶችን ለወደፊት ጥቅም ላይ ለማዋል እድል ይሰጣል። የመጨረሻው የህክምና ምርጫ ውሳኔ እንደ ሀኪሙ እና ለማዳመጥ፣ ለመተንተን እና ከታካሚው ሁኔታ ጋር የተጣጣሙ መፍትሄዎችን ለመስጠት ባለው ችሎታ ላይ የተመሰረተ ይሆናል፡፡
ይህ ሁሉ የመካንነት ህክምና ስኬት ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል?
እውነተኛ የህይወት ታሪክ ዘመናዊ ቴክኒኮች፣ የላብራቶሪ ልህቀት እና ግለሰብን ማዕከል ያደረገ አቀራረብ ምን ያህል ለስኬት ሚስጥራዊ መሳሪያዎች እንደሆኑ ያሳያል። የአቺባደም ኮዝያታጊ ሆስፒታል ፕሮፌሰር ሴም ፊቺቺዮግሉ እንዲህ ይላሉ:- “46 ዓመቷ ነበር እናም ከዚህ ቀደም አምስት ያልተሳካ የ መካንነት ህክምና (IVF) አድርጋለች። ወደ እኔ ስትመጣ የእንቁላል ክምችት መጠኗ በጣም ቀንሷል። መጀመሪያ ላይ እንቁላሎችን ለማነቃቃት ጥረት አደረግን። ከዚያም የእርሷን ሁኔታ ታሳቢ ያደገ መደበኛ የPGS IVF መካንነት ህክምና ጀመርንላት፡፡ አንድ መደበኛ ፅንስ አስተላለፍንላት እና አረገዘች። ባለፈው ሳምንት ወንድ ልጅ እንዳገኘች የምስራች ሰማን። እድሜዋን ግምት ውስጥ ከገባ ይህ በእውነት ድንቅ ነው፡፡ ጤናማ ሕፃን በራሷ እንቁላል፡፡ መልካም ዜና!”
በቱርክ ካሉ ባለሞያዎቻችን ነፃ የህክምና አስተያየት ለማግኘት አሁን ያግኙን



